A BOOK REVIEW ON “MY MEMORIES”

A BOOK REVIEW ON “MY MEMORIES”

Publication Date : 02/03/2025


Author(s) :

Daniel Kassahun Waktola.


Volume/Issue :
Volume 14
,
Issue 1
(03 - 2025)



Abstract :

ዓለምአንተ ገብረሥላሴ የልጅነትና የዩኒቨርሲቲ ትውስታውን፣ የመሬት ይዞታ ጥናትና እና የመሬት ላራሹ አዋጅ ተሳትፎውን፣ በትግራይና በበጌምድር የነበረውን የትጥቅ ትግሉን፣ በሱዳን እና በፈረንሳይ ያሳለፈውን የስደት ዘመኑን፣ በአሜሪካ የኖረበትን አካዳሚያዊና ፖለቲካዊ ሕይወቱን፣ ወዘተ በ“ትውስታዎቼ” መጽሐፉ አካቷል። ሆኖም በጥልቀትና በስፋት የተዳሰሰው ጉዳይ የመሬት ይዞታ ጥናትና እና የመሬት ላራሹ አዋጅ ተሳትፎውን በመሆኑ የዚህ የመጽሐፍ ዳሰሳ በመሬት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። የዓለምአንተ ትውስታዎቼ ከተለመዱ ግለ ታሪኮች ለየት ይላል። በሥር ነቀሉ የገጠር መሬት አዋጅ መረቀቅና መተግበር ላይ የነበረውን የግል እና የቡድን ተሳትፎውን ተመርኩዞ፤ በአዋጁ ዙሪያ ሲቀርቡ ከቆዩ የተሳሳቱ ትችቶችና ትርክቶች መክቷል። አከራካሪ ሆነው የቆዩ ጉዳዮችን ደግሞ በጊዜ ሂደት ነጥረው በወጡ ፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚያዊ ዕይታዎች አንፃር ቃኝቶ ለአንባቢ አቅርቧል። ስለሆነም መጽሐፉ እንደሚከተለው ጠለቅ እና ሰፋ ያለ ዳሰሳን ጋብዟል።


No. of Downloads :

0